አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ምልከታ አድርገዋል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በተቋሙ የበለፀጉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ስራዎችን መገምገሙንና በኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውሮ መመልከቱን ከኢንስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢንስቲትዩቱን ስራዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ዝርዝር ማብራሪያ ማቅረባቸውም ተገልጿል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከዕድሜው በላይ የሆኑ ስራዎች መስራቱን የሱፐርቪዥን ቡድኑ መሪ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አንስተው ተቋሙ ለሀገር ትልቅ አቅም እንደሆነ መጠቆማቸውም ተመላክቷል፡፡
ይህን አቅም በተለያዩ ዘርፎች ለሚታዩ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ በበለፀጉ የቴክኖሎጂ ስራዎች የብዙኃንን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር ኢንስቲትዩቱ በቅንጅት ስለሚሰራበት አግባብ በሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት ጥያቄዎች ቀርበው በዋና ዳይሬክተሩ ምላሽ እንደተሰጣቸውም ተገልጿል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025