አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ተጀምሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይዳ ምዝገባ አፈፃፀም ግምገማና የተማሪዎች የምዝገባ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በትብብር እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025