
ባህርዳር፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ግብርን በወቅቱ በመክፈል በአገራችን ልማት ላይ አሻራችንን የማሳረፉን ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአማራ ክልል ምስጉን ግብር ከፋዮች ገለጹ።
በባህር ዳር የሚገኘው የኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የምንከፍለው ግብር ለጤና፣ ለትምህርት፣ለመንገድና ለተለያዩ የልማት ስራዎች እየዋለ መሆኑን ተገንዝበናል።
ግብር መክፈል ክብር፣ግብርን መሰወር ግን የሃገርን እድገት እንደሚጎዳ በመረዳት ከስወራ መታቀብ እንደሚገባም አቶ ዳንኤል መክረዋል።
ይህን በመረዳትም ሪዞርታቸው በ2016 በጀት ዓመት ካገኘው ገቢ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ግብር በመክፈል እውቅናና ሽልማት ማግኘቱን አስረድተዋል።
ግብራቸውን በፍትሃዊነት ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ባለሃብቶች እንደዚህ አይነት እውቅና መሰጠቱ በህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን ወደ ህጋዊነት ለመመለስ አስተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።
የአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል የፋይናንስ ኃላፊ አቶ አማረ አያሌው በበኩላቸው፥ ለእውቅናና ሽልማት የበቁት ግብር የዜግነት ግዴታ መሆኑን በመገንዘብም ከድርጅቱና ከሰራተኞች የሚሰበሰበውን በፍላጎትና በራስ ተነሳሽነት መክፈል በመቻላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
የእውቅና ሽልማት መሰጠቱ አበረታች ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመው፥ የግብር አከፋፈል ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን ደመመ እንደገለጹት ባለፉት ሰባት ወራት በቅርንጫፉ ከ5 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ለሃገር ልማት አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።
ለዚህ ግብር መሰብሰብ ግንባር ቀደም የሆኑና የህግ ተገዥነትን በማክበር ሀገራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ ምስጉን ግብር ከፋዮች እውቅና መስጠት ጀግናን ከማክበር የተለየ አይደለም ብለዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮና ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሰሞኑን ያካሄደውን የምስጉን ግብር ከፋዮች የእውቅናና የሽልማት ስነ ስርዓት መካሄዱ ይታወሳል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026