ጭሮ ፤የካቲት 22/2017 (ኢዜአ)፡-የጭሮ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ የተመረቁበትን ሙያ ወደ ተግባር ለመለወጥ ዕድል እንደፈጠረላቸው የከተማው ወጣቶች ገለጹ፡፡
በማህበር ተደራጅተው በኮሪደር ልማቱ የስራ ዕድል ያገኙ የከተማው ወጣቶች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተመረቁበት ሙያ በኮሪደር ልማቱ ስራ በመሰማራት ገቢ ከማግኘታቸውም በላይ ሙያቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ እድል አግኝተዋል፡፡
በኮሪደር ልማቱ ስራ ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል ጀማል ኑሬ አህመድ፤ ከጅማ ዩኒቨርስቲ በስቪል ምህንድስና በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቋል፡፡
ወጣቱ እንደሚለው በከተማ ማዘመን፣ በመንገድ መሰረተ ልማትና መሰል ሙያዎች የቀሰመውን ትምህርት ወደ ተግባር ለመለወጥ የኮሪደር ልማቱ እድል ፈጥሮለታል፡፡
መንግስት በኮሪደር ልማት የተሻለ ከተማ ለመፍጠር እየሰራ ያለው ስራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ ለማድረግና ቱሪዝምን ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግሯል፡፡
በዩኒቨርስቲ የቀሰመውን ሙያ ወደ ተግባር በመለወጥ በኮሪደር ልማቱ የበኩሉን አስተዋጽዎ እያበረከተ መሆኑን ገልጿል።
ከጨርጨር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግንባታ ሙያ የተመረቀው ወጣት ሻፊ መሀመድ በበኩሉ የኮሪደር ልማቱ ከስራ ዕድል ፈጠራ በተጨማሪ ሙያውን ለማሳደግ ዕድል ፈጥሮለታል፡፡
''በኮሪደር ልማቱ በንቃት በመሳተፍ አሻራዬን ለማኖር እሰራሁ ነው'' ያለው ወጣቱ በቀጣይ በትላልቅ የግንባታ መስኮች ለመሰማራት ራዕይ እንዳለው ተናግሯል፡፡
በኮሪደር ልማቱ የተከናወኑ የመንገድ ዳር ማስዋብ፤ የአረንጓዴ ልማት እና መሰል ስራዎች በትምህርት የቀሰመውን ሙያ በተግባር ለማዳበር ትልቅ አስተዋጽዎ እያበረከተለት መሆኑን የተናገረው ደግሞ ሌላኛው ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሰርቬይንግ ትምህርት መስክ በዲፕሎማ የተመረቀው ወጣት የሱፍ ቀመር ነው፡፡
''በኮሪደር ልማቱ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከሙያዬ ጋር ተያያዥ ናቸው'' ያለው ወጣቱ ይህም ሙያውን እንዲያሳድግ አስተዋጽዎ እንደፈጠርለት ተናግሯል፡፡
''የኮሪደር ልማት ከፈጠረልኝ የስራ ዕድል ባለፈ ተጨማሪ ሙያዎችን እንድለምድ እያገዘኝ ነው'' ብሏል ወጣቱ፡፡
የጭሮ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት የስራ ዕድል ፈጠራና ክትትል ቡድን መሪ አቶ ወርቅነህ ተስፋዬ እንደገለጹት በበጀት አመቱ 437 ወጣቶች የኮሪደር ልማትና ተያያዥ በሆነ የግንባታ መስክ በ23 ማህበራት ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡
በማህበራት ከተደራጁት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ወጣቶች ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው በኮሪደር ልማቱ የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
ወጣቶቹ በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ስልጠናዎች እና ሌሎች ድጋፎች እንደተደረገላቸው አመልክተዋል፡፡
የጭሮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ጎሳዬ በበኩላቸው በከተማው የመንገድ ዳር ውበትና፣ አነስተኛ ድልድዮችና አደባባይ ግንባታን ያካተተ የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
በኮሪደር ልማቱ ነዋሪዎች የመንገድ ዳር ትርፍ ይዞታዎችን በማንሳት እንዲሁም ባለሀብቶች በንግድ ቤቶቻቸው ፊትለፊት የሚከናውን የእግረኛ መንገድ ለማስዋብ ቃል መግባታቸውን አመልክተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025