የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የሸገር ከተማ ዘመናዊነትን ጠብቆ ለማልማት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት ይሰራል

Mar 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ የሸገር ከተማን በታቀደው መሰረት ዘመናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለማልማት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት ይሰራል ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የፋይናንስ ተቋማትና የሸገር ከተማ አስተዳደር ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄዷል።

ከንቲባው በመድረኩ ላይ ሸገር ከተማ በሀሳብና በአደረጃጀት ዘመኑን በሚመጥን መልኩ የሚመራ ከተማ ነው ብለዋል።

ከተማው ከተመሰረተ ጀምሮ አስፈላጊ ዝግጅቶች ሲያደርግ ቆይቶ አሁን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተለይ በመሬት አጠቃቀም፣ የከተማ አስተዳደሩ የሚመራባቸው ህጎችና ስርዓቶች እንዲሁም ለአንድ ዘመናዊ ከተማ የሚያስፈልጉ ሂደቶች አየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ሂደት የባለሀብቶችና የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው አስተዳደሩ ወሳኝ ከሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በዚህም የኢንቨስትመንት እድሎችን ጨምሮ በከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን አመልክተዋል።

በዛሬው መድረክም ከተማውን በተሻለ መልኩ ለመምራትና ለማስተዳደር ከትልልቅ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ውይይት መደረጉን አስረድተዋል።

በቀጣይም ከተማ አስተዳደሩ የተሻለች ከተማን እውን ለማድረግ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025