ሀዋሳ፤ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ)፦ የይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እሴት የተጨመረባቸውን የግብርና ምርቶች በማምረት በዘርፉ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን በፓርክ የተሰማሩ ኩባንያዎች ገለጹ።
ምቹ መሰረተ ልማት ያሟላው ፓርኩ፤ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን በመትከል ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግና የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዳስቻለም ተናግረዋል።
ኢዜአ ካነጋገራቸው ባለሀብቶች መካከል የጎልደን ኦርጋኒክ ኦይልና የፋሚሊ ሃኒ ፋብሪካ ባለቤት ኢንጂነር ዘላለም ወልደአማኑኤል በፓርኩ አቮካዶና ማር የሚያቀነባብሩ ሁለት ፋብሪካዎቻቸውን ወደሥራ አስገብተዋል።
ባለሀብቱ እንዳሉት ከአቮካዶ ዘይት ፋብሪካው ብቻ በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ያቀዱ ሲሆን እሴት የተጨመረበት የማር ምርት ለማቀነባበርም እየሰሩ ነው።
ለፋብሪካዎቹ ግብዓት የሚያቀርበውን የእርሻ ፕሮጀክት ጨምሮ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ወደ ማቀነባበር ሥራ መግባታቸውንም ኢንጂነር ዘላለም አስረድተዋል።
ከአቮካዶና የማር ምርት ከሚያቀርቡ ከ110 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር መፈጠሩን ገልጸው፣ በዚህም ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የሔብሮን ኮፊ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሮምዮ ዛራሜላ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ ዕሴት የተጨረበት ቡና ወደ ውጭ ለመላክ እየተንቀሰቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።
ፋብሪካው በቀን እስከ 2 ሺህ ኪሎ ግራም ቡና የመቁላት ዕቅድ እንዳለው ጠቅሰው፤ ከ10 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር ለአርሶ አደሮችም ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ስለመሆኑ አንስተዋል።
የ'ኢትዮ ፍሩት ፋብሪካ" መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብዙነህ ጉታ በበኩላቸው በቀን 80 ቶን አቮካዶ ዘይት የሚያመርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በፓርክ ውስጥ ተክለዋል።
ፋብሪካው ለሚጠቀመው ግብዓት ከስምንት ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠሩን ጠቁመዋል።
ባለሀብቶቹ እንደሚሉት ፓርኩ መሰረተ ልማት ያሟላ በመሆኑ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች በቀላሉ ለማምረት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል።
ይህም ለዘርፉ እመርታና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አንስተዋል።
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሃይሉ የተራ እንዳሉት እስካሁን በግብርና ምርቶች ማቀነባበር የተሰማሩ ስምንት ፋብሪካዎች ወደስራ ገብተዋል።
ከነዚህም መካከል አራቱ በአቮካዶ ዘይት ምርት መሰማራታቸውን ገልፀው፤ የአቮካዶ ጥሬ ምርቶችን ከአርሶ አደሩ በመረከብ የገበያ ትስስር እንደፈጠሩ ገልጸዋል፡፡
ባለፉት አምስት ዓመታት ከ2 ሺህ 664 ቶን በላይ እሴት የተጨመረበት የአቮካዶ ዘይት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 17 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማስገኘታቸውን እንዲሁ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025