
አዲስ አበባ፤ የካቲት30/2017(ኢዜአ)፦ የመከላከያ አጠቃላይ አቅሞች ኢትዮጵያ እያንሰራራች እና አስተማማኝ አቅም ላይ እንዳለች በግልጽ እንደሚያመላክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ኢትዮጵያን ለመጠበቅ የሚያስችል ከፍተኛ ብቃት እንዳለ የሚያረጋግጥም ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪን ዛሬ መርቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንዱስትሪውን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ዛሬ እየተመረቱ ያሉ ድሮኖች ከጥቂት ዓመታት በፊት ለማምረት የማይታሰቡ እንደነበሩ አውስተዋል።
በትልም መልክ ተቀምጠው የነበሩ አዳዲስ የጦር አቅሞች እና አቅም አባዢ መሳሪያዎችን በራስ ገንዘብ ገዝቶ ለመታጠቅ አዳጋች እንደነበር ገልጸዋል።
ሰው አልባ ድሮኖች ተግዝተው ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላም በሚፈለገው አቅም ለመጠቀም ውስነነቶች እንደነበሩም ተናግረዋል።
በዓለም ደረጃ የውጊያ መልክ ተቀይሮ ወደ አራተኛው ትውልድ ጦርነት እየተገባ መሆኑ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በሌሎች ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች አቅምን ማጉልበት ቁልፍ መሆኑ ታምኖበት በመንግስት በኩል በከፍተኛ ትኩረት ሲሰራበት መቆየቱን አመልክተዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ትጋት በተከናወነ ስራ በኢትዮጵያዊያን እውቀት፣ የሰው ኃይል እና የቴክኖሎጂ አቅም የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ማምረት መቻል መጀመሩ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የታገዙት ድሮኖች ጦርነትን ማስቀረት ብቻ ሳይሆን ጦርነትን ባጠረ ጊዜ ለመጨረስ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
ቴክኖሎጂው ለመከላከያ፣ የፖሊስ ኃይል እና ደህንነት ዘርፉ ተደማሪ አቅምን የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል።
ቴክኖሎጂ በባህሪው ሁልጊዜ አዳጊ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርምርን ማስቀጠል፣ ገበያን ማምጣት እና የተቋማትን የቅንጅት አሰራር ማጎልበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
መንግስት በስትራቴጂው ኢትዮጵያ በዓለም የድሮን ገበያ ድርሻ እንዲኖራት ማስቀመጡንና ይህንንም እውን ለማድረግ ገበያን ማፈላለግ አበክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የመከላከያ አጠቃላይ አቅሞች ኢትዮጵያ እያንሰራራች እና አስተማማኝ አቅም ላይ እንዳለች በግልጽ እንደሚያመላክቱ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን ለመጠበቅ የሚያስችል ከፍተኛ ብቃት እንዳለ የሚያረጋግጥም ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያላትን አቅም አሟጦ በመጠቀም ያላትን ከፍታ ለማላቅ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ብልጽግናን እውን ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026