
ያሉንን እምቅ ሃብቶች ማልማት ከተቻለ ከራስ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ የሚያስችል ሰፊ እድል መኖሩን በተግባር አረጋግጠናል - ሴት አርሶ አደሮች
ጋምቤላ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- ያሉንን እምቅ ሃብቶች ማልማት ከተቻለ ከራስ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ የሚያስችል ሰፊ እድል መኖሩን በተግባር አረጋግጠናል ሲሉ በጋምቤላ ክልል በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ሴት አርሶ አደሮች ተናገሩ።
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል።
እለቱን በማስመልከትም በጋምቤላ ወረዳ የሴት አርሶ አደሮች የመስኖ ልማት ስራዎች በፌዴራል ከፍተኛ ሴት አመራሮች ተጎብኝቷል።

ያሉንን እምቅ ሃብቶች ማልማት ከተቻለ ከራስ አልፎ ለሌሎችም መትረፍ የሚያስችል ሰፊ እድል መኖሩን በተግባር አረጋግጠናል ሲሉም ተናግረዋል።
ከአርሶ አደሮቹ መካከል አሪያት ፍቅሩ፣ መስራት ከተቻለ ሀገርን መለወጥ የሚያስችል እምቅ ሃብት አለን ብለዋል።
እርሳቸው እያለሙት ባለው የሰብልና የጓሮ አትክልት ልማት ከእራሳቸው ፍጆታ አልፈው ሌሎችም እየደገፉና የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላኛዋ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማሩት ወይዘሮ ቻም ኡጆር፣ በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰፊ መሬት ማልማት ከተቻለ የሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ለውጭ ገበያ የሚተርፍ ሰፊ ምርት የሚገኝበት መሆኑን ገልፀዋል።

አርሶ አደር ፈቲያ አሊ፣ የግብርና ስራ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥና ህይወትን በቀላሉ የሚለውጥ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል።
በዘርፉ የጀመሩትን ልማቶች በማጠናከር አምራቾችና ላኪዎች ለመሆን መዘጋጀታቸውን አርሶ አደሮቹ አረጋግጠዋል።
ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነትና የህገ መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ፣ በክልሉ በግብርና ልማት የተሠማሩ ሴት አርሶ አደሮች ተሞክሮ ለሌሎች አካባቢዎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ለተሻለ ስኬት እንዲሰሩ አስገንዝበው የሁሉም እገዛና ድጋፍ እንዳይለያቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አሪያት ኡጁሉ፣ የአርሶ አደሮቹ ጥረት የሚደነቅና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ መንግስት በኩል ለአርሶ አደሮቹ ቀጣይነት ያለው አስፈላጊው ድጋፍና እገዛ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።
በክልሉ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ሁነቶች ዛሬ ተከብሯል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026