
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2017(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል በመስራት ይቻላልን በተግባር ያሳየነውን ያህል ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ማዕከሉ 205 ቢሊዮን የተፈቀደ ካፒታል እንዳለው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ለአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በስኬት መጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ያዘጋጀው የእውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ የማዕከሉ ግንባታ የተጀመረው ከለውጡ በፊት ቢሆንም በተጨባጭ ተግባራዊ የተደረገው በለውጡ መንግስት ነው።

የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ስራዎችን በተናጠል ማከናወን ከባድ፤ በጋራ ሲከናወኑ ደግሞ ቀላል እንደሆኑ በተግባር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የማዕከሉ ግንባታ ወጭ 96 ነጥብ 2 በመቶ በከተማ አስተዳደሩ የተገነባ መሆኑን አውስተው፤ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች ተቋማትም ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል 40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ፤ 21 የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ከእኛ ሀገር ይቀድማል ብለው ቦታቸውን ለቀውልናል ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ማዕከል መገንባት የተቻለው በቅን ኢትዮጵያውያን የላቀ ትጋትና ትብብር መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም አዲስ አበባን የአፍሪካ የስበት ማዕከል ማድረግ የሚያስችል ማዕከል እንዲገነባ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የመገናኛ ብዙሃን፣ የፀጥታ አካላት፣ ሌሎች በሂደቱ የተሳተፉ የመንግስትና የግል ተቋማት ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል መስራት እንደምንችል አሳይተንበታል ያሉት ከንቲባዋ በማዕከሉ ተጠቃሚነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች እንደገለጹት፤ ማዕከሉ 205 ቢሊዮን የተፈቀደ ካፒታል አለው።
ኢትዮጵያውያን የማዕከሉን አክሲዮን በመግዛት ለስኬታማነቱ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026