የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለወጣቶች ክህሎት ልማት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው

Mar 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 01/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢኮኖሚ ስብራትን በመጠገን ለወጣቶች ክህሎት ልማት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢንዱስትሪ እና የክህሎት ልማት ሥራ ለሀገር ዕድገት የማይነጣጠል ሚና እንዳላቸውም በመድረኩ ተገልጿል።


በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት "ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች" በሚል መሪ ሀሳብ "ክህሎት ስለ ኢትዮጵያ" ምዕራፍ ሁለት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፥ "በክህሎት የበቃ የሰው ሃይል፥ ለአንድ ሀገር ምን አስተዋጽኦ ይኖረዋል" በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

በጽሁፋቸው ጥራት ያለው ክህሎት የተላበሰ ዜጋን ማፍራት ለአንድ ሀገር የጋራ ትርክት ግንባታ ወሳኝ ጉዳዮች መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የሀገርን የለውጥ ጉዞ ለማሳካት ገበያ-መር ክህሎትን የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢኮኖሚያዊ ስብራትን ለመጠገንና ለወጣቶች ክህሎት ልማት ቁልፍ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

የወጣቶችን ክህሎት የበለጠ ለማበልጸግና ለሀገር ዕድገት ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ ከአምራች ኢንዳስትሪና ከግሉ ዘርፍ አልሚዎች ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተግባር ተኮር የትምህርትና ስልጠና ርዕይን እውን ለማድረግ ሕጋዊ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተባባሪ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራበት መሆኑንም አስረድተዋል።

የመንግስትና የግል ተቋማት በክህሎት ልማት ትብብራቸውን በማጠናከር የኢትዮጵያን ዕድገት የሚያስቀጥል ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት የበለጠ እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

ኢንዳስትሪ እና ክህሎት ልማትን የሚዳስስ የውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የኢንዱስትሪ እና የክህሎት ልማት ሥራ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የማይነጣጠል ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።


የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የሚፈልገውን ክህሎት የተላበሰ የሰው ሃይል ለማፍራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅና ሌሎች ዘርፎች የሚሰሩ የኢንዱስትሪ የሚኒስቴር የስልጠና ማዕከላትም ክህሎት የተላበሰ የሰው ሃይል ለማፍራት አዎንታዊ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የኢንዳስትሪ አቅም ግንባታ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ክህሎት መር የግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ኢንዳስትሪ ልማትን ለማሳለጥ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በብዝሃ ኢኮኖሚ ልማት ለኢንዱስትሪ ምርታማነት የተሰጠው ትኩረትም በተኪ ምርት ላይ ውጤት በማስመዝገብ የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለማስቀረት የሚያስችል መደላድል እየተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026