
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የትራፊክ አደጋ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ማዘመን የሚያስችል ሶፍትዌር ስራ አስጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ስራ ላይ የዋለውን ሶፍትዌር በተመለከተ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀማል አባሶ በመግለጫው፤ ባለፉት የለውጥ አመታት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡
በዚህም በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ይደርስ የነበረው የትራፊክ አደጋ ትርጉም ባለው መልኩ ቅናሽ ማሳየቱን ገልጸው፣ ለዚህም የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ እንደነበር አመላክተዋል፡፡
ነግር ግን በመረጃ አያያዝ ስርዓት ላይ ክፍተቶች አንደነበሩ አንስተው፤ ይፋ የተደረገው ሶፈትዌር ክፍተቶችን በመሙላት የመረጃ አሰባሰብ ስርዓቱን ወደ ዲጂታል የሚቀይር ነው ብለዋል፡፡
ሶፍትዌሩ የመረጃ ታዓማኒነትን የሚያረጋግጥ፣ ጊዜን የሚቆጥብ እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሶፍትዌሩ ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሙከራ ላይ መቆየቱን ተናግረው፤ በዚህም አስተማማኝነቱ ተረጋግጧል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኢንተለጀንስ ዋና መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ሐብታሙ ካሳ በበኩላቸው፤ ሶፍትዌሩን ለማበልጸግ ሁለት አመታት እንደፈጀ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው እለት ስራ ላይ የዋለው ሶፍትዌር የትራፊክ አደጋ ከደረሰበት ስፍራ መረጃ በቀጥታ ወደ ፌደራል ፖሊስ የመረጃ ቋት እንደሚያስገባ ተናግረዋል።
አዲሱ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስርዓት እንደ ጤና ተቋማትና ሌሎች መሰል ባለድርሻ አካላት የመረጃ ቋት ጋር የተሳሰረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2022 ዓ.ም የአፍሪካ ምርጥ የፖሊስ ተቋም ለመሆን የያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ እንደሚያግዝም ተናግረዋል።
ሁለቱ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ማዘመን የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026