
ወልዲያ ፤ መጋቢት 1/2017 (ኢዜአ) ፡- መንግስት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች ውጤት የታየባቸው መሆናቸውን በሰሜን ወሎ ዞን የጉባላፍቶ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።
በዞኑ በጉባላፍቶ ምርጫ ክልል በህዝብ የተወከሉ የክልል ምክር ቤት ተመራጮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በወልዲያ ከተማ ምክክር አድርገዋል።
በምክክሩም መንግስት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
በውይይቱ ላይም የሃራ ከተማው ነዋሪ አቶ ወርቁ ይመር እንዳሉት በከተማዋ ዘርፈ ብዙ የልማት ውጤቶች በመመዝገባቸው ነዋሪውን ተጠቃሚ እያደረጉ ናቸው።
በተለይም የከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመብራት አገልግሎት እንዲሁም የኮሪደር ልማት ስራዎች አበረታች ውጤት ማሳየታቸውን አንስተዋል።
ሌላው የጉባላፍቶ ወረዳ ነዋሪ አቶ ይመር ንጉስ በበኩላቸው በወልዲያ ከተማ የሚገነቡት የአስፋልትና የቀለበት መንገድ ስራዎች የከተማዋን እድገት የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል።
እነዚህም መንግስት ልማትን በማፋጠን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በነዳጅ ላይ የሚስተዋለውን ህገወጥ እንቅስቃሴ፣ የኑሮ ውድነትና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መንግስት እንዲፈታ የጠየቁት ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊ አቶ እሸቱ ተክሌ ናቸው።

የወልዲያ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ንጉስ ዝናቡ በበኩላቸው ተሳታፊዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ህዝብና መንግስት እየተመካከሩ በጋራ የሚፈቷቸው ናቸው ብለዋል።
የኑሮ ውድነትን ለመፍታት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እየቀረቡ መሆናቸውን ጠቁመው ህገወጥ ነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠር አዲስ አሰራር ተተግብሯል ብለዋል።
በአማራ ክልል ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባልና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ወይዘሮ አስናቀች ኃይሌ እንዳሉት የክልልና የተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር መወያየታቸው ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ ነው።

በመድረኩ የተነሱ መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚያግዙ አስረድተዋል።
መንግስት ህዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንዲችልም ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት መሪ ተዋናይ እንዲሆን ጠይቀዋል።
በጉባ ላፍቶ ምርጫ ክልል ስር የጉባላፍቶና የአንጎት ወረዳዎች እንዲሁም የወልዲያና የሃራ ከተሞች እንደሚገኙም ተመልክቷል።
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026