ቦንጋ፤መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፦በክልሉ በበልግ ወቅት 359 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የአዝርዕት ሰብሎች እንደሚለማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው ምክትል ሀላፊና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ እንዳሉት፥ የበልግ እርሻን ውጤታማ ለማድረግ የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም እየተሰራ ነው።
በበልግ እርሻ በቆሎ፣ቦሎቄ፣ሩዝ፣ ማሽላና በሌሎች ሰብሎች ከሚለማው 359 ሺህ ሄክታር መሬት ከ13 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ለማምረት መታቀዱን ተናግረዋል።
እስካሁንም ከ173 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማረስ 25 ሺህ ሄክታሩ በበቆሎ ሰብል መሸፈኑን ገልፀዋል።
ከበልግ ማሳ 30 በመቶው በኩታ ገጠም ለማልማት መታቀዱን ገልጸው፣ ለልማቱም 156 ሺህ 300 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እንዲሁም ምርጥ ዘር መቅረቡን አስታውቀዋል።
በክልሉ ካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ በበልግ አዝመራ በተለያዩ ሰብሎች 8ሺህ 650 ሄክታር ማሳ በማልማት 311 ሺህ 400 ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የወረዳው ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ መንገሻ ናቸው።
እስካሁኑ ከ6 ሺህ ሄታር በላይ ማሳ መታረሱን ጠቁመው፥ አጠቃላይ ከሚለማው ማሳም 7 ሺህ 36 ሄክታሩ በበቆሎ እንደሚሸፈን አመልክተዋል።
በወረዳው የጨበራ ቀበሌ አርሶ አደር አየለች አባጊሶ በበኩላቸው፥ ግማሽ ሄክታር ማሳቸውን በበልግ እርሻ በበቆሎ ሰብል በመሸፈን 60 ኩንታል ለማምረት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
በግብርና ባለሙያዎችና በየደረጃው ባሉ አመራሮች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህም የተሻለ ምርት ለማምረት ያስችለኛል ብለዋል።
ሌላው የቀበሌው አርሶ አደር ናስር አባቡልጉ፥ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ተጠቅመው በሁለት ሄክታር ማሳ በቆሎ ለማምረት የእርሻ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንና 80 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
የዝናብ መዘግየት ሥራው በተወሰነ ጊዜ ዘግይቶ እንዲጀመር ማድረጉን ጠቁመው፣ አሁን መጣል የጀመረውን ዝናብ ተጠቅመው ማሳቸውን በዘር እንደሚሸፍኑ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025