
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፦ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ሀገራዊ ፋይዳ የሚቀይሩባቸውን ማዕከላት እና የፈጠራ ስነምህዳሩን ምቹ ማድረግ እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
አህመዲን አህመድ (ዶ/ር) ከአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር በመሆን በስልጠና ላይ የሚገኙ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች (ስታርትአፖችን) ጎብኝተዋል።
ዶክተር አህመዲን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ቴክኖሎጂ የሥራ ፈጠራና ክህሎት ለውጥ መሪ ቁልፍ በመሆኑ ዘርፉን ማበረታታት፣ የወጣቶችን ዕምቅ ችሎታ ወደ ተግባር የሚቀይሩበትን አመቺ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
እየተሰጠ ያለው ስልጠናም የወጣቶችን የፈጠራ ሃሳብ የሚያጠናክርና ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢንስቲትዩቱ የሚገኘውን ሜከርስፔስ (BiTec) የሚገኙ ከሀሳብ ጀምሮ ወደ ስራ የገቡ የተለያዩ ችግር ፈች የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጎብኘታቸውን አመልክተዋል።
ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ሀገራዊ ፋይዳ የሚቀይሩበትን ማዕከላት እና የፈጠራ ስነምህዳሩን ምቹ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ዶክተር አህመዲን፤ በስልጠናው ከፍተኛ ሚና ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችን አመስግነዋል።
ለስታርትኦፕች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል በመልዕክታቸው።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026