ወጣት ፌደሳ ሹማና ወጣት ሄኖክ ግርማ ለኤሌክትሪክ ስራ ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራቸው በሚኖሩበት አካባቢ የኤሌክትሪክ ብልሽት ሲኖር የጥገና ስራዎችን በመስራት ወላጆቻቸውን ሲያግዙ ቆይተዋል።
ፌደሳ ሹማ ትውልድና እድገቱ በቄለም ወለጋ ዞን ደንቢዶሎ አካባቢ ሲሆን ከህፃንነቱ ጀምሮ ህይወቱን ለማሸነፍ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል።
ወጣቱ በትውልድ ቦታው የተመለከተው ችግር በኤሌክትሪክ ሃይል ዙሪያ የተለየ ፍላጎትና ትኩረት እንዲሰጥ መነሻ እንደሆነውም ያስታውሳል።
በመኖሪያ ቀዬው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና ሱቅ ከፍቶ ይሰራ በነበረበት ጊዜ በተደጋጋሚ በሚያጋጥመው የመብራት መቆራረጥ ስራው ይስተጓጎል እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ይህን ተከትሎ ስራውን ለማሻሻል የሚረዳውን ጄነሬተር መጠቀም ቢጀምርም የነዳጅ ወጪው ከፍተኛ መሆንና ከጀኔሬተሩ የሚወጣው ድምጽ አካባቢውን መረበሹ መፍትሄ እንዲፈልግ አነሳስቶታል፡፡
በዚህም ነዳጅ የማይጠቀምና ድምፅ አልባ ጄነሬተር ለመስራት መነሳሳት እንደፈጠረበት በማስታወስ ከተደጋጋሚ ጥረት በኋላ ሙከራው ተሳክቶለት ፈጠራውን እውን ማድረግ ችሏል፡፡
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የፈጠራ ሃሳብና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ስልጠና በሚወስዱበት ሰመር ካምፕ መግባቱና ለሁለት ዓመታት ያክል ስልጠና መውሰዱ በፈጠራ ስራው ላይ በርካታ ማሻሻያዎችን ለማድረግ አስችሎታል።
ባደረገው ማሻሻያ ጄነሬተሩን አንድ ጊዜ ቻርጅ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ አንድ ወር ያለመቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ በመቻሉ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች እየተጠቀሙበት መሆኑን አንስቷል።
አሁን ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ትእዛዝ እየቀረበላቸው መሆኑን ጠቅሶ ለአብነት የጁቡቲ ባለሃብቶች ምርቱ እንዲቀርብላቸው ያሳዩትን ፍላጎት ተከትሎ ንግግር መጀመራቸውን ጠቁሟል።
ወጣት ፌደሳ የሰራው የፈጠራ ስራ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተከትሎ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እየቀረበ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ጄነሬተሩ የድምጽ ብክለት የማያስከትልና በቻርጅ የሚሰራ በመሆኑ ለነዳጅ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ የሚያስቀር ነው ብሏል፡፡
ሄኖክ አማኑኤል በቢውልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት መመረቁን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ውድድሮች ተሳትፎው አሸናፊ በመሆን የተለያዩ ሽልማቶች መቀበሉን ይናገራል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው ስልጠና ላይ ከፌደሳ ጋር መተዋወቃቸውን ያስታወሰው ሄኖክ አብረው ቢሰሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ በማመን ወደ ስራ መግባታቸው አስታውሷል።
ምርታቸውን ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን ተከትሎ ባገኙት ምላሽ በመበረታታት በቀጣይ ኢትዮጵያን የሚያስጠራ ምርት በማምረት ወደ ውጭ የመላክ ህልም እንዳላችው ተናግሯል።
የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን(ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ አጫጭርና ረጃጅም ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
ኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞቹ ያላቸውን የፈጠራ ችሎታ እንዲያዳብሩ እንዲሁም ማሻሻል ያለባቸውን ጉዳይ በማስተካከል ሃሳባቸው መሬት ወርዶ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ያደረጋል ።
በፈጠራ የዳበረውን ጄነሬተር እውን ያደረገው ወጣት ፌደሳ ተቆጥሮ የማያልቀው የፈጠራ ባለቤትነቱ እንዳስደነቃቸው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
ጄነሬተሩ አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ለበርካታ ቀናት መቆየት የሚችል በመሆኑ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ይችላል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025