የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን በቁርጠኝነት ይሰራል - ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር)

Mar 15, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ።

ዋና ፀሐፊው ከወቅቱ የኢጋድ ሊቀ መንበር እና የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው 43ኛው የኢጋድ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ውጤቶች ላይ ያተኮረ ነበር።


ዋና ጸሀፊው ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በውይይቱ በጉባዔው ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች ተግባራዊነት እና ኢጋድ ቀጣናዊ ፈተናዎችን ለመፍታት ያለው ቁርጠኝነት ላይ ከሊቀመንበሩ ጋር ሀሳቦች እንደተለዋወጡ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሙሉ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

አስቸኳይ ጉባኤውን ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ኃይሎች አለመግባባቶችን በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ኢጋድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025