አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምቹ የቴክኖሎጂ ስነ ምህዳር ያላት አገር ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሦስተኛው ዙር የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሽፕ 2025 ውድድር በሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል።
በውድድሩ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የሚወዳደሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ባሉ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ አፍሪካውያን ተማሪዎችም ተሳትፈውበታል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ኢትዮጵያ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች ነው።
የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በዲጂታል ዘርፍ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር መሰራቱን አንስተው ይህም በዘርፉ ያለውን ክህሎትና እውቀት ለማዳበርና የፈጠራ ሃሳብን ለማበርከት ማገዙን ጠቁመዋል።
የቴክኖሎጂን ተደራሽነት፣ አካታችነትና ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዘርፉ ከምስራቅ አፍሪካ ብሎም ከአፍሪካ ምቹ ስነምህዳር ያላት አገር ለማድረግ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል።
ከአለም አቀፍ መስፈርትና ከአገሪቱ መሪ የልማት እቅድ ጋር የተናበበ ምቹ ስነምህዳር ለመፍጠር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።
በዘርፉ ያሉ ተዋናዮችን በማሳደግ ያሉ ሀብትና እውቀትን በማልማት ኢትዮጵያን የሚያስጠሩ ዜጎች ለማፍራት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ለዲጂታል ክህሎት ልማት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
የዲጂታል መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የግሉ ዘርፍ ለዲጂታል ልማት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚያስችል ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል።
ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ሂሳብና ምህንድስና ትኩረት በመስጠት ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።
የአፍሪካ ሮቦቲክስ ውድድር ፈጠራን የሚደግፉ ስራዎች የሚታዩበት እንደሆነና ሃሳብን በማልማትና በማሳደግ እንዲሁም ወደተግባር በመለወጥ ሀብትና የስራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
የኢትዮ ሮቦቲክስ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናክሬም መኮንን በበኩላቸው፤ ውድድሩ የተማሪዎችን የፕሮግራሚንግ፣ ዲዛይን፣ ምህንድስና እና ተዛማጅ ክህሎቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ በዘርፉ ስራዎችን ሲያከናውን 15 አመት ማስቆጠሩን ገልፀው እስካሁን ባለው ተወዳዳሪዎች ከአገር ውስጥ ባለፈ በተለያዩ የአለም አገራት ኢትዮጵያን በመወከል መወዳደር ችለዋል ብለዋል።
ውድድሩ አገራዊ አበርክቶው ከፍ እንዲል ከመንግሥት ጋር በትብብር እየሰራን ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በቀጣይም ውድድሩን በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ግብ ይዘናል ለዚህም አስፈላጊው ድጋፍ እንሻለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በውድድሩ የተሳተፉት ዊዳድ አብደላና ማቲያስ ዮናስ በሮቦቲክስ ዘርፍ ከአገር ውስጥ አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድረው አገራቸውን ማስጠራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025