የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ዓለም-አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር እየተሰራ ነው

Mar 15, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦መንግስት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ISO 21001/2018 ለመተግበርና የሙያ ብቃት ምዘና እና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በመታገዝ አውቶሜት ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።


በስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከላትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።


የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ለመተግበር ባከናወነው ስራ ውጤቶች መገኘታቸውን አመልክተዋል።


በዚህም ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችሉ ተቋማት መፈጠራቸውንና አዳዲስ ተቋማት ከቀድሞዎቹ ልምድ በመውሰድ ራሳቸውን የማሻሻል ስራ እያከናወኑ ይገኛል ብለዋል።


ሚኒስትር ዴኤታው ተቋማት የጥራት ሥራ አመራር ስርዓቱን በሚጠበቀው ደረጃ ለመተግበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025