
አዲስ አበባ፤መጋቢት 5/2017 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያዘጋጀው 57ኛው አህጉራዊ የኢኮኖሚ ልማት፣የገንዘብና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
“የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን፤ አፈጻጸሙን የሚያልቁ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን መቀየስ” የጉባዔው መሪ ሀሳብ ነው።
በጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ፣ ፋይናንስ እና ፕላን ባለሙያዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ የውይይቱ ዋንኛ አጀንዳ ነው።
ባለፉት ቀናት በጉባዔው ላይ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ ስኬታማ ለማድረግ የአፍሪካ ሀገራት፣ የግሉ ዘርፍ እና ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተነስቷል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
የስምምነቱን ትግበራን ለማፋጠን የጋራ ጥረት ትብብርና ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ አመልክተዋል።
ዲጂታላይዜሽን፣የምግብ ዋስትና እና የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን ሌሎች የጉባዔው የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
በባለሙያዎች ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል። ባለሙያዎቹ ሚኒስትሮቹ የሚወያዩባቸውን አጀንዳዎች ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉባዔው በሚኒስትሮች ደረጃ መጋቢት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በጉባዔው መሪ ሀሳብ ላይ ከፍተኛ የፖሊሲ ምክክር መድረክ ያደርጋሉ።
በተጨማሪም ከጉባዔው ጋር የተጓዳኙ የተለያዩ ሁነቶች መጋቢት 6 እና 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚደረጉም ኢዜአ ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026