የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የክልሉ መንግስት የቡና እና ቅመማቅመም ምርት ጥራትና ምርታማነት በማሳደግ ወደ ውጪ መላክ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ እየሰራ ይገኛል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

Mar 17, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- የክልሉ መንግስት የቡና እና ቅመማቅመም ምርት ጥራትና ምርታማነት በማሳደግ ወደ ውጪ መላክ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተግባሪ ግብረ ሀይል የ2017 ግማሽ ዓመት የቡና ጥራት አጠባበቅና አቅርቦት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የክለሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የለውጡ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲውን ከአንድ ዘርፍ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ሲያሻግር፥ ግብርናን ዋነኛ የኢኮኖሚው መሠረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።


የክልሉ መንግስትም ግብርናን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የክልሉ ኢኮኖሚ መሠረት በማድረግ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የኤክስፖርት ምርቶች በማምረት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም የክልሉን እምቅ አቅም በመለየትና በመጠቀም የቡና እና ቅመማቅመም ምርት ጥራትና ምርታማነት በማሳደግ ወደ ውጪ መላክ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ክልሉ የይርጋጨፌ፥ የአማሮ እና ሌሎችም ባለ ልዩ ጣዕም ጥራት ያላቸው ቡናዎች የሚበቅሉበት መሆኑን ጠቁመው ዘርፉ የውጪ ምንዛሬ በማስገኝት ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብለዋል።


የቡና ማሳን በማስፋትና በመጠንና በጥራት ተወዳዳሪ መሆን የሚችል ቡና በማምረት አርሶ አደሩ ባመረተው ልክ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ታአማኒ፥ በገበያ ተፈላጊና ተወዳዳሪ የሆነ ጥራት ያለው ቡና በአርሶ አደሮች በስፋት እንዲመረት የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተግባሪ ግብረ ሀይሉ ተጠናክሮ መስራት አለበት ብለዋል።

በቅርቡ በኢትዮ ቻይና የልማት ትብብር በተፈጠረ የንግድ ትስስር ጥራት ያለው የይርጋጨፌ ቡና ወደ ቻይና ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ተሞክሮው ወደ ሌሎች ቡና አምራች አካባቢዎች መስፋት አለበት ብለዋል።


በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በበኩላቸው ክልሉ ቡናን ኤክስፖርት በማድረግ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የቡና ምርት በሁሉም ስነምህዳሮች የሚበቅል ብቻ ሳይሆን በእርሻ ላይ ለሌሎች የግብርና ስራዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሰብል መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በ2017 ዓም 25 ሺህ 884 ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡንም ጨምረው መናገራቸውን ከክልሉ ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025