አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቋሚ የስራ ዘርፎች በማሸጋገር በኩል ውጤታማ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
በመዲናዋ በልማታዊ ሴፍትኔት የተመዘገቡ ስኬቶች ለሌሎች ከተሞችም ተሞክሮ እንደሚሆን ተመላክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ 154ሺህ 923 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና የስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ፕሮግራሙን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ለሶስተኛ ዙር በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ ይደረጋል።
ቀደም ሲል ተግባራዊ በተደረጉ ሁለት ዙሮች ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቋሚ የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ በማድረግ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በዚህም በመጀመሪያው ዙር ከ415ሺህ በላይ በሁለተኛው ደግሞ 107 ሺህ የሚደርሱ ተጠቃሚዎች በመርሃ ግብሩ መመረቃቸውን አንስተዋል።
በሶስተኛ ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች በከተማዋ የልማት ስራዎች ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያገኙት ገቢ በመቆጠብ ወደ ቋሚ ስራ ለመሸጋገር ማቀድ እንዳለባቸውም አስረድተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በሶስተኛው ዙር የሚሳተፋ የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎች በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና የስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
መርሃ ግብሩ በኢትየጵያ መንግስት ሙሉ ወጪ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም የቢሮ ሀላፊ አስታውቀዋል፡፡
ተጠቃሚዎቹ ለቀጣይ ሶስት አመታት በጽዳት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በከተማ ግብርና እና በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለከተማው እድገት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል፡፡
ልማታዊ ሴፍትኔት ከተረጂነት ለመላቀቅ ለሚደረገው ጉዞ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የተናገሩት ደግሞ በየካ ክፍለ ከተማ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑት ናስር አሊ ናቸው።
በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ በመሆናቸው መደሰታቸውንና በቀጣይ ኑሯቸውን ለመለወጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በምትሰራው ስራ የምታገኘውን ገቢ በአግባቡ በመቆጠብ ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር መዘጋጀቷን የተናገረችው ሌላዋ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ገነት ብርሃኑ ነች።
የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በከተማዋ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ገቢያቸውን በመቆጠብ ወደ ቋሚ የስራ እድል የሚሸጋገሩበት ፕሮግራም መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025