ሚዛን አማን፣መጋቢት 7/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የምዕራብ ኦሞ ዞን ሠላምን አስጠብቆ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጎልበቱ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገለጸ ።
በዞኑ ሠላምና ልማት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ዛሬ በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ርዕስ መስተዳደረ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤በዞኑ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ሕዝቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።
በአካባቢው የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚጠናከር ጠቁመው፤ የልማትና የሠላም ግንባታ ሥራዎች ላይ የማኅበረሠቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው፤ አመራሩ ዋጋ ከፍሎ የሕዝቡን ሠላም ለማስጠበቅና የልማት ፍላጎት ለማሟላት መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የአካባቢው ወጣቶች በእርሻና ሌሎች የሥራ ዘርፎች ተደራጅተው በመሠማራት የሥራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ለዚህም በተለያዩ ምዕራፎች ማኅበረሠቡን ያሳተፈ የምክክር መድረክ በዞኑ ሁሉም መዋቅሮች እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው፥የአካባቢውን ሠላም ለማፅናትና አብሮነትን ለማጠናከር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ ፤ በምክክሩ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ወደ ተግባር ለመቀየር ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ያሉንን እምቅ ሀብቶች በጋራ አልምተን ሕዝባችንን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት አድርገን እንሰራለን ሲሉም አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025