ሀዋሳ፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በክልሉ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ባለፉት አራት ዓመታት የጋራ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው በመከናወናቸው ውጤት መምጣቱንም ገልጸዋል።
በክልሉ በመንገድ፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎትና በሌሎች ዘርፎች ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውንም አቶ ደስታ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ቤተሰብን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል የቤተሰብ ብልፅግና መርሀ ግብር ተቀርፆ ወደ ትግበራ መገባቱን ጠቁመዋል።
መርሃ ግብሩ በውስጡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮችና ፓኬጆች እንዳሉትም ነው የገለጹት።
የክልሉን ጸጋዎች በመጠቀም ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህም በርካቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ለአብነትም ባለፉት አራት ዓመታት በክልሉ ለ300 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ጠቁመው የሥራ ፈጠራ ዘርፍ እንዲጠናከር በሥራ መነሻ ካፒታል፣ በመስሪያ ቦታና በተለያየ መንገድ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።
ምርትና ምርታማነትን ትርጉም ባለው መልኩ በማሳደግ ገበያን የማረጋጋት ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የመንግስትንና የህዝብን አቅም በማስተባበር በከተሞችና በገጠር እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች በህዝብ ተጠቃሚነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆኑንም ገልጸዋል።
እንደ አቶ ደስታ ገለጻ የኮሪደር ልማት ሥራው ከተሞችን ምቹና ተወዳዳሪ ከማድረግ ባለፈ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል የቀየረና ለበርካቶችም የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።
ህዝቡ በክልሉ ባለው የሰላምና የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ አመራርም ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ሆኖም ልማቱ የማይዋጥላቸው ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጠቅመው የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነታው የራቀ በመሆኑ በህዝቡ ዘንድ ተቀበይነት እንዳላገኘም አቶ ደስታ በመግለጫቸው አያይዘው ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025