አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሲኤ) እና የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) በተለያዩ መስኮች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።
በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።
ኢሲኤ እና ፋኦ ከጉባዔው ጎን ለጎን በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በአፍሪካ የዘላቂ ግብርና እና የግብርና ንግድ ልማት፣ የምግብ እና የስነ ምግብ ዋስትናን ማረገገጥ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸው ነው።
የኢሲኤ የፕሮግራም ድጋፍ ምክትል ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ ስምምነቱን ጊዜውን የጠበቀ ሲሉ ገልጸውታል።
ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዘላቂ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና እና የምግብ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025