የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

እ.አ.አ በ2030 የአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ መጠን 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ተመላከተ

Apr 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2017(ኢዜአ)፦ እ.አ.አ በ2030 የአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ መጠን 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላከተ።

በማስተር ካርድ የፋይናንስ ድጋፍ ጄነሲስ አናሊቲክስ የተሰኘ የአፍሪካ የኢኮኖሚ አማካሪ ተቋም ባወጣው ሪፖርት የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በፈጣን የኢንተርኔት ተደራሽነት እና ፋይናንስ አካታችነት በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ገልጿል።

የኢንተርኔት አቅርቦት ማደግ እና የፋይናንስ አካታችነት በአፍሪካ የዲጂታል ክፍያ እንዲሰፋ ያደረጉ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ በሪፖርቱ መመላከቱን የዘ ኢስት አፍሪካን ዘገባ ያመለክታል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፤ በአህጉሪቱ የኢንተርኔት ተደራሽነት በየዓመቱ በ20 በመቶ እና የፋይናንስ አካታችነት በየዓመቱ 6 በመቶ እድገት እንደሚያሳይ ይጠበቃል።


የማስተር ካርድ የምስራቅ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪዮስ ዶሲስ አፍሪካ እምቅ አቅሞች አሏት፤ ህዝቡም በቀጣይ አስርት ዓመታት የዓለምን ኢኮኖሚ በመቅረጽ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልጸዋል።

ተቋሙ የአፍሪካን የፋይናንስ ደህንነት እና ኢኮኖሚ እድገት በሚያረጋገጡ የዲጂታል፣ ኢኖቬሽንና የመንግስትና የግል አጋርነት ላይ መዋዕለ ንዋዩን እንደሚያፈስ አመልክተዋል።

የማስተር ካርድ የአፍሪካ ቀጣና ፕሬዝዳንት ማርክ ኤሊዮት አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን ኢኮኖሚ እያስመዘገቡ ያሉ ሀገራት የሚገኙበት አህጉር መሆኑን ገልጸው ለአህጉሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ እና ሙያዊ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የጄነሲስ አናሊቲክስ በሪፖርቱ ቢሻሻሉ ያላቸውን የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችንም አቅርቧል።

የአፍሪካ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ምጣኔን ማሳደግ፣ ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጦችን ቀልጣፋ ማድረግ እና የንግድ ስራ ምቹነት ማሻሻል እንደሚገባ መግለጹን ዘ ኢስት አፍሪካን በመረጃው አስፍሯል።

ኢትዮጵያም በሀገር ውስጥ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመዘርጋት ድንበር ተሻጋሪ የኢ-ኮሜርስ ንግድን ማሳለጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቅርቡ አስታውቋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞን የሚያሳልጡ የኢ-ኮሜርስና የኤሌክትሮኒክ ስትራቴጂዎች ጸድቀው ሥራ ላይ መዋላቸውንም እንዲሁ፡፡

ዲጂታል ቴክኖሎጂ የአፍሪካን ኢኮኖሚ መልክ የሚቀይር፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥርና አፍሪካ በዓለም ገበያ ያላትን ድርሻ የሚወስን መሆኑም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025