
አዲስ አበባ፤መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፡-የአፍሪካን የባህር እና የመጠጥ ውሃ ሀብቶች ያለውን ቀጣናዊ ትብብር ማጠናከርን ያለመው የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ ለማፅደቅ የተዘጋጀው አውደ ጥናት ዛሬ በታንዛኒያ ዳሬሰላም መካሄድ ጀምሯል።
ስብስባውን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም በጋራ በመተባበር ነው።
የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ የአፍሪካን የባህር እና የመጠጥ ውሃ ሀብቶች የሀገራት እና የዘርፉ ተዋንያን ትብብር ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
እ.አ.አ በ2023 በአሜሪካ ኒው ዮርክ የተፈረመው ዓለም አቀፍ የባህር ብዝሃ ህይወት ዘላቂ አጠቃቀም ስምምነት (BBNJ Agreement) የትግበራ አፈጻጸም ሌላኛው የአውደ ጥናቱ የመወያያ አጀንዳ ነው።
የአፍሪካ ሀገራት እ.አ.አ ጁን 2025 በፈረንሳይ ኒስ በሚካሄደው ሶስተማው የተባበሩት መንግስታት የውቅያኖስ ኮንፍረንስ ላይ ይዘው የሚቀርቡትን የጋራ አቋም ይፋ እንደሚያደርጉ የህብረቱ መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ የውቅያኖስ አስተዳደር ስትራቴጂ ለማፅደቅ የሚደረገው አውደ ጥናት እስከ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026