ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- በምሥራቅ ጎጃም ዞን በበጀት ዓመቱ እስካሁን ድረስ ከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ማር ተመርቶ ለገበያ መቅረቡን የዞኑ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በጽሕፈት ቤቱ የንብ ሃብት ባለሙያ አቶ ስማቸው ደምሴ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየለማ ያለው ደን ንብ በማነብ የማር ምርታማነትን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
በዚህም በያዝነው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ ማር ለማምረት ታቅዶ እስካሁን ከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ ማምረት መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ ሚሊዮን ኪሎ ግራም ማር በላይ ብልጫ አለው ብለዋል።
የማር ምርቱን መሰብሰብ የተቻለውም ከ240 ሺህ በላይ ዘመናዊ፣ ባህላዊና ሽግግር ቀፎዎች ከሚገኘው የንብ መንጋ መሆኑን አስታውቀዋል።
የማር ምርታማነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ መምጣቱን የገለጹት አቶ ስማቸው፤ ለዚህም የደንና የበጋ መስኖ ልማቱ ንቦች የሚቅስሟቸው የአበባ ዛፎች በስፋት እንዲገኙ በማስቻሉ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥ እቅዱን ሙሉ በሙሉ በማሳካት የአምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሙያዊ እገዛ እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የአዋበል ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ገድፍ ይታይህ በሰጡት አስተያየት፤ በዚህ ዓመት ከአስር የሽግግርና ዘመናዊ ቀፎ ንብ ከ110 ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት ማግኘት ችያለሁ ብለዋል።
ከሶስት የሽግግርና ከስድስት ባህላዊ ቀፎዎች በዓመት ከ60 ኪሎ ግራም በላይ ምርት እያገኙ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአነደድ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ሙሉቀን የቆየ ናቸው።
በዚህ ዓመትም እስካሁን ባለው ከ40 ኪሎ ግራም በላይ ለገበያ አቅርበው ከ25ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን አስረድተዋል።
ከእንስሳትና አሳ ሃብት ተጠሪ ጽሕፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባለፈው ዓመት ከአንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት ለገበያ ቀርቧል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025