በአካባቢው እምብዛም ይታወቅ ያልነበረውን የቡና ልማት ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የፍራፍሬ ዝርያዎችን ለፍሬ በማብቃታቸው በምሳሌነት የሚጠቀሱ አርሶ አደር መሆን ችለዋል።
የአርሶ አደሩ ተግባር በተመሳሳይ የልማት ስራ ላይ ለሚሰማሩ ሌሎች አርሶ አደሮች ጥሩ ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ስለመሆናቸውም ተነስትል።
አርሶ አደር መኮንን ተኹሉ በላዕላይ ማይጨው ወረዳ የ"መዶገ" ገጠር ቀበሌ ማህበር ነዋሪ ናቸው። አርሶ አደሩ ወራጅ ወንዝን በመጥለፍና ተዳፋት የሆኑ ቦታዎችን በማስተካከል አትክልትና ፍራፍሬን ማምረት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል።
ዘይቱንን ጨምሮ ሌሎች ፍራፍሬዎችን፣ የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ስራ ላይ መቆየታቸውን የሚናገሩት አርሶ አደሩ ከግብርና ባለሙያዎች ባገኙት ሙያዊ ድጋፍም ወደ ቡና ተክል፣ አፕል፣ ማንጎና አቮካዶ ፍራፍሬዎች መሸጋገራቸውን ገልፀዋል።
አሁን ላይም 250 የቡና ችግኞችን ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ የአቮካዶ፣ የማንጎና የአፕል ተክሎችን በመስኖ እያለሙ መሆኑን የገለጹት አርሶ አደር መኮንን ለገበያ በማቅረብም ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ ተናግረዋል።
በሚያገኙት ገቢም ሁለት ልጆቻቸውን በመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ ግብር ማስመረቃቸውን ገልጸዋል።
በመስኖ ልማት ባገኙት ገቢም የእህል ወፍጮ ከመትከል በተጨማሪ በንብ እርባታ ዘርፍ መሰማራት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በአክሱሞ ዩኒቨርሲቲ የሽሬ ካምፓስ እርሻ ኮሌጅ የእፅዋት ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ አባዲ ብርሃነ (ዶ/ር) በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የተመለከቱት የመስኖ ልማት ለሌሎች አርሶ አደሮችና በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አርዓያ ሊሆን የሚችል ነው ብለዋል።
አርሶ አደሩ በተለይ በቡና ምርት ላይ ያሳዩት የስራ ተነሳሽነትን ሌሎች አርሶ አደሮች ወደ ተግባር ቢቀይሩት በዘላቂነት ከድህነት መውጣት እንደሚያስችላቸው አመልክተዋል።
በክልሉ በቡና ምርት ውጤታማ ከሚባሉ አካባቢዎች ሽሬ እንዳስላሴ፣ እንዳባጉና፣ ተምቤን፣ አክሱም እና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች ተጠቃሽ መሆናቸውንም ተመራማሪው ገልጸዋል።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የላዕላይ ማይጨው ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ፅህፈት ቤት የኤክስቴንሽን ባለሙያ አቶ ሙሉ አየለ፣ አርሶ አደሩ የቡና ልማት ከጀመሩ ወዲህ ውጤታማና የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እንዳገዛቸው ተናግረዋል።
የአርሶ ደሩ ተግባር በአካባቢያቸው ውሃ እያለ ወደ ልማት መቀየር ላልቻሉ አርሶ አደሮች ተነሳሽነትን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
አርሶ አደር መኮንን የቡና ችግኝን ጨምሮ ከሚያመርቱት አትክልትና ፍራፍሬ 100 ያህል ችግኞችን ለሌሎች 10 አርሶ አደሮች በነጻ ከማከፋፈል ባለፈ ለመስኖ ልማት የሚውል ጥልቅ ጉድጓድ በአንድ ሚሊዮን ብር ወጪ ማስቆፈራቸውም በመልካም ተግባር የሚጠቀስላቸው ተግባር ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025