
አዳማ፤መጋቢት 25/2017(ኢዜአ )፦አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚያስችል ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የጀመረውን ጥረት ማጠናከሩን ገለጸ።
ዩኒቨርሲቲው በሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ) ዘርፍ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ መሆኑም ገልጿል።
በዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ምህንድስናና ኮምፒዩቲንግ ኮሌጅ ዲን ተክሉ ዑርጌሳ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚችሉ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበቁና የሰለጠኑ ዜጎችን ለማፍራት እየሰራ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በተለይ ከኢትዮጵያ አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ከስልጠናዎቹ መካከል ከአራት ዓመት በፊት በሁለቱ ተቋማት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት በሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ይገኛል ብለዋል።
ከሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሩ ባሻገር ዩኒቨርሲቲው በአርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ለተማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ነው ያሉት።
ከዚህም ባለፈ በኢንስቲትዩቱ የተለዩ ቁልፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይ በግብርና፣በጤና፣በሚቲዎሮሎጂን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ በዩኒቨርስቲው ስልጠና እየወሰዱ በሚገኙ ሰልጣኞች የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ብቻ ሳይሆን በኮምፒውተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ልዩ የጥናትና ምርምር ቡድን በማደራጀት በዳታ ሳይንስ፣በኮምፕውተር ቪዥንና ሮቦቲክስ፣ በክላውድ ኮምፒዩቲንግና ዲስትሪቡዩቲንግ ሲስተም የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በተመሳሳይም በኔትዎርኪንግና ስማርት ሶፍትዌር ሲስተም ላይ ያተኮሩ የምርምር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፥ የምርምር ስራዎቹ በዩኒቨርሲቲውና ከውጭ በሚገኝ የፕሮጀክት ፋይናንስ ድጋፍ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026