አዲስ አበባ፤መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፡-በአስር የፌዴራል ተቋማት፣ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እየተገነቡ ያሉ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ እየተጠናቀቁ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጹ፡፡
የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ዘመናዊ ስማርት ስክሪን፣ ስማርት ላይቲንግ፣ የተሻሻሉ የቴሌ እና የቪዲዮ ኮንፈረንሶችን ማድረግ የሚያስችሉ፣ የኔትወርክ፣ የድምፅ ብክለትን የሚቀንሱ መሳሪያዎች፣ ምቹ ክፍሎች፣ የአየር ማቀዝቀዣ የተገጠሙላቸው ናቸው።
ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት በ5 የፌደራል ተቋማት የተገነቡ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ተመርቀው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ዶ/ር)፤ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ወጪና ጊዜን የሚቆጥቡ ዘመናዊ ናቸው ብለዋል፡፡
የስማርት ክፍሎቹ የተለያዩ ስብሰባዎችንና ስልጠናዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ እንዲሁም በጽሑፍ ለማስረዳት የሚረዱ ዲጂታል ኋይት ቦርዶችን ያካተቱ መሆኑንመ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በ5 ተቋማት ተገብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረው 24 ተጨማሪ ስማርት ክፍሎችን በክልሎችና በተመረጡ የፌዴራል ተቋማት የመገንባት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በዓለም ባንክ 4 ሚሊዮን ዶላር በጀት እየተከናወነ ያለው የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ አንድ አመት መፍጀቱን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በክልሎች፣በከተማ አስተዳደሮችና በ10 የፌዴራል ተቋማት እየተገነቡ ያሉ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።
በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሳይበር ሴኩሪቲ ኢኒጂነር ሱራፌል ዲሪባ ለኢዜአ እንዳሉት፥ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሉ በቴክኖሎጂ የተደራጀ ከመሆኑ ባለፈ እስከ 25 ሰዎች በአንድ ላይ መሰብሰብ የሚቸሉበት ነው።
ክፍሉ ያለ ኔትወርክ መቆራረጥ ስብሰባን ለማድረግ የሚያስችልና የመረጃ ደህንነትን ከመጠበቅ አኳያ ሚናው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025