የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ በወርቅ ማዕድን ላይ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የምርትና የገቢ መጠንን ማሳደግ ተችሏል

Apr 7, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ ፤መጋቢት 27/2017 (ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በወርቅ ማዕድን ላይ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የምርትና የገቢ መጠንን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው፤ በክልሉ በተለይም የወርቅ ምርት እንቅስቃሴን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በክልሉ ወርቅ፣ የድንጋይ ከሰልና ሌሎችም እምቅ የማዕድን ሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰው በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በወርቅ ምርት ላይ ይስተዋል የነበረውን ህገ ወጥ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የምርትና የገቢ መጠንን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 105 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ መቻሉን ጠቅሰው በቀጣይም ጥብቅ ቁጥጥሮችን በማድረግ ህጋዊ አሰራሮች ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።


የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገብረ መስቀል ሰጠኝ፤ በክልሉ የወርቅ ማዕድን ሃብት በብዛትና በስፋት መኖሩን አንስተው በህጋዊ አሰራር ለሀገር ጥቅም እንዲውል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዘርፉ ልማት ፈቃድ የተሰጣቸው 165 የወርቅ አምራች ማህበራት በስራ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው አዳዲስ የወርቅ ማዕድን ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ፍቃድ በመስጠት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።


የምዕራብ ኦሞ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዜናው አለማየሁ፤ በወርቅ ማዕድን ላይ የሚስተዋለውን ህገ ወጥነት የማስቆም ስራ በትብብርና በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025