አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተሰሩ ተግባራት በመዲናዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እንዳደረጋቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2017 የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደርዕይ ከፍተዋል።
አውደ ርዕዩ "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መር ሃሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ አስተዳደሩ ቀዳሚ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ነው።
በመሆኑም የዘርፉን ተግዳሮት በመፍታት ከተማዋን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በዚህም ከተማዋን የኢንዱስትሪ ማዕከል በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል፡።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመዲናዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ምርታማነት በማሳደግ በኩል አስተዋጾኦው ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው መንግስት የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ሂደት የአምራች ኢንዱስትሪው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ገቢ ምርትን በመተካት እና ኤክስፖርትን በማሳደግ፣ የሥራ ዕድልን መፍጠር ጨምሮ የቴክኖሎጅ ሽግግርን ለማሳለጥ አይተኬ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘርፉ እያከናወነ ያለው ስራ እንደሀገር ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መሰረተ ልማቶችን በማሟላት፣ የፋይናንስና ማሽነሪ አቅርቦት በማሳደግ እንዲሁም ማስፋፊያ ቦታዎችን በማቅረብ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም በአስተዳደሩ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከነበረበት 48 በመቶ ወደ 64 በመቶ እንዲያድግ ማስቻሉን ጠቅሰዋል።
በአውደ ርዕዩ ምርታቸውን ያቀረቡት የአሚዮ ኢንጂነሪንግ የኢንዱስትሪና እርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ ባለቤት ሙዘሚል መሐመድ አውደርዕዩ የገበያን ትስስር ለመፍጠር ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ኬር ኤይዚ የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም መራዊ እና ገረመው ጠቅላላ የፋውንደሪ ማምረቻ ኩባንያ ባለቤት ገረመው አህመድ በበኩላቸው አውድርዕዩ ምርቶችን በማስተዋወቅ ከደንበኞች ጋር ለመገናኘት ያስችላል ብለዋል።
በአውደ ርዕዩ 250 የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025