የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተደረጉ ማሻሻያዎች ውጤት እያመጡ ነው - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

Apr 8, 2025

IDOPRESS

መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተደረጉ ማሻሻያዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ አንድ ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች እና ለማህበራት አስረክቧል።


አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅቱ እንደገለጹት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤታማ የማሻሻያ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

ከዚህ በፊት ለአርሶ አደሩ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማነቆ የነበሩ አሰራሮችን በማሻሻል በግብርና ዘርፍ እድገት እየተመዘገበ መሆኑን አመልክተዋል።

ለአብነት ከዚህ በፊት ትራክተሮችና ሌሎች የግብርና መሳሪያዎች ከውጭ ሲገቡ ከፍተኛ ቀረጥ ይጣልባቸው እንደነበር ጠቅሰው አሁን ላይ የግብርና መሳሪያዎችን ከታክስ ነፃ በሆነ መንገድ በማስገባት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡


የክልሉ አርሶ አደር የእርሻ መሳሪያዎችን በብድር እንዲያገኝ እድል መመቻቸቱንም ጠቅሰዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ በበኩላቸው በክልሉ በትኩረት እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል የግብርና ሜካናይዜሽን አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በተሰሩ ሥራዎች በምርትና ምርታማነት እድገት ላይ ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰዋል።


እስካሁን ሻሸመኔ በሚገኘው በኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻ በኩል ብቻ ከ3ሺህ 500 በላይ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች፣ ለማህበራትና ለሌሎች ማስረከብ እንደተቻለ ጠቅሰው በአሁን ወቅት በክልሉ 8ሺህ ትራክተሮች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ትራክተር ከተረከቡ አርሶ አደሮች መካከል በቦረና ዞን የድሬ ወረዳ ነዋሪው ካራ ዳባቲቻ አስር አርሶ አደሮች ሆነው በኩታ ገጠም ከ20 ሄክታር በላይ መሬት እያለሙ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን በበሬ እንደሚያርሱ ገልጸዋል።


አሁን ያገኘነው ትራክተር፣ ጉልበትና ጊዜያችንን ቆጥበን በወቅቱ አርሰን በወቅቱ እንድንዘራና ምርታማ እንድንሆን ያስችለናል ብለዋል።

በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የሀዊ አባያ ማህበር ሊቀ መንበር ወጣት አየናቸው አለማየሁ በበኩሉ ለአስር ሆነው በ35 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ አዝርዕትና አትክልቶችን እያመረቱ መሆኑን ተናግሯል።

እስካሁን ትራክተር በመከራየት እንደሚያርሱ ገልጾ አሁን ያገኘነው ትራክተር በሥራችን ላይ መነሳሳት የሚፈጥርልን ነው ብሏል፡፡

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም አርሶ አደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025