አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017 (ኢዜአ)፦የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድር ሂደቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማሳካት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የድርድር ቡድኑ ዋና ተደራዳሪ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የዓለም ንግድ ድርጅት ብሄራዊ የድርድር ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል።
በቅርቡ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት 5ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ቆይታ የነበረው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ልዑካን ቡድን ከተሳካ ቆይታ በኋላ ወደ ሃገር ቤት መመለሱ የሚታወስ ነው።
ይህን ተከትሎም የተደራዳሪ ቡድኑ በያዝነው ዓመት በወርሃ ሀምሌ ለሚካሄደው 6ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
በዛሬው የኮሚቴው ስብሰባ ከአባል ሃገራት ጋር በሚደረጉ የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነቶች እንዲሁም የ6ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ የዝግጅት ስራዎችና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል።
በ6ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ድርድሩን የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ ሁኔታ፣ በከፍተኛ ትኩረትና በበቂ ዝግጅት ለማካሄድ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የድርድር ቡድኑ ዋና ተደራዳሪ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ናቸው።
የድርድር ሂደቱን በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማሳካት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
እ.አ.አ በ2026 ካሜሮን በሚካሄደው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ የኢትዮጽያ የአባልነት ሂደት ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ በመረጃው አመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025