
መቀሌ፤ሚያዝያ 1/2017 (ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል ማይጨው ወረዳ በ13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የመንግስት በጀት የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛና ሰርቶ ማሳያ ማእከል እየተገነባ መሆኑ ተገለጸ።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማእከላት ማጠናከርና ክትትል አስተባባሪ ተክላይ አብርሃ፤የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛና ሰርቶ ማሳያ ማእከላትን እንቅስቃሴና የግንባታ ስራ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም፥ በክልሉ ማይጨው ወረዳ የፌዴራል መንግስት በመደበው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በጀት ዘመናዊ የሆነ አዲስ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛና ሰርቶ ማሳያ ማእከል ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
የማእከሉ ግንባታ በሶስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት የሚበቃ ሲሆን ለ15 ሺህ አርሶ አደሮች አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።
ማእከሉ በዋነኝነት በእርሻ ኤክስቴንሽን፣በእንስሳት ሃብት ልማትና ተዋጽኦ፣በንብ ማነብና በማር ምርት፣በዶሮ እርባታና ሌሎችም መስኮች ስልጠና እንደሚሰጥም አመልክተዋል።
በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ 600 ማእከላትም በመልሶ ግንባታና ግብዓቶችን በማሟላት ወደ አገልግሎት መግባታቸውም ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026