
አዳማ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ሸዋ ዞን የወተት ላሞችን ዝርያ በማሻሻል የወተት ምርታማነትን የማሳደግ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በዞኑ የማር ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻልም 14 ሺህ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱም ተመላክቷል።
የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ 101 ሺህ ላሞችን በሰው ሰራሽ ዘዴ ለማዳቀል ታቅዶ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 98 ሺህ ላሞችን ማዳቀል ተችሏል።
የወተት ላሞችን ዝርያ በማሻሻል፣ ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት፣ ግብዓት በማሟላትና ዝርያቸውን በመለየት የወተት ምርትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም በወተት ልማት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶና አርብቶ አደሮች፣ በግልና በማህበር የተደራጁ ሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚ ናቸው ብለዋል።
አሁን ላይ የወተት ምርት እያደገ ቢሆንመ ካለው የህዝብ ብዛትና ፍላጎት ጋር አለመመጣጠኑን ጠቅሰው ለዚህም ዝርያቸውን የማሻሻልና የጤና እንክብካቤ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ጊደሮችና ላሞችን ሴት ጥጃዎችን ብቻ እንዲወልዱ የሚያደርግ ቴክኖሎጂን እንዲሁም ሆርሞኖችን ጥቅም ላይ ለማዋል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
የእንስሳቱ አመጋገብ ካልተሻሻለ የዝርያ ማሻሻል ስራ ብቻውን ለውጥ ሊያመጣ ስለማይችል የመኖ ልማትን በየደረጃው በማስፋፋት አቅርቦቱን ለማሟላት ተቀዳሚ ተግባር ተደርጎ እየተሰራ ስለመሆኑም አክለዋል።
በሌላ በኩል በዞኑ የማር ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ነው አቶ አብነት የገለጹት።
በያመቱ የዘመናዊ ቀፎዎችን ስርጭት ለማሳደግ እየተሰራ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ወራት ብቻ 14 ሺህ ዘመናዊ ቀፎዎች ለልማቱ ተሳታፊዎች ተሰራጭተዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026