
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 2/2017 (ኢዜአ)፦ ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት ሊቆጠብ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ።
ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት አጠራጣሪ መልዕክት ሲያገኝ ለተቋሙ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ያስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የጥንቃቄ መልዕክት ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች!
የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ አድራሻዎች ለሀገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በይበልጥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አካዉንቶችን በመንጠቅ ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አረጋግጧል። ከተለያዩ አካላት በቴሌግራም የሚደርሱን ሊንኮች በርካታ አደጋዎችን የሚይዙ ሲሆን የሚከተሉት አደጋዎች በዋናነት ይገኙበታል፡

የግል መረጃ መጠለፍ:- እንደ የባንክ መለያ ወይም የይለፍ ቃል ያሉ መረጃዎችን መሰረቅ፤

የማልዌር ስርጭት:- ስልኮችን ወይም ኮምፒውተሮችን የሚጎዱ ቫይረሶች፤

ማጭበርበሪያ:- ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ ተስፋዎች (እንደ ውርርድ ወይም ኢንቨስትመንት) መታለል፤
በመሆኑም ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ እያሳሰብን፤ ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና በፍጹም ልንከፍታቸዉ ከማይገቡ ሊንኮች መካከል የሚከተሉት ከታች በምስሉ ያሰፈርናቸዉ ይገኙበታል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቴሌግራማችን አጠራጣሪ የሆኑ ሊንኮች ካጋጠመን ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሚከተሉት አድራሻዎች ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
• e-mail: [email protected]
• ነጻ የስልክ መስመር፡ 933
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026