የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

114 ተጨማሪ ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ተጠቃሚ ሆኑ

Apr 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 3/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ዞን፣አርሲ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ ዞን እና ምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 114 ተጨማሪ ከተሞች የላቀ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ።


ኩባንያው አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ የመገንባት ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።


ኢትዮ ቴሌኮም ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በደቡብ ምስራቅ ሪጂን 58 እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን 56 በድምሩ 114 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረጉን አመልክቷል።


የሞባይል ኔትወርኩ የላቀ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ አዳዲስ ዕድሎችን በመክፈት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።


ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት ፍጥነት በመላ ኢትዮጵያ በማስፋፋት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመረጃው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025