አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሎጂስቲክስ ዘርፍ ተመራጭ መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ገለጹ፡፡
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትስስርን ታሳቢ በማድረግ ለሎጂስቲክስ ዘርፉ መዘመን ትኩረት መሰጠቱንም ገልጸዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ደንጌ ቦሩ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሎጂስቲክስ ዘርፍ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይ ባለፉት ስድስት አመታት ዘርፉን ለማሻሻል እና ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀርጾ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
በዚህም ዘርፉን በማሻሻል በኩል አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ለመሆን የተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ስርዓት ወሳኝ በመሆኑ ዘመኑ የደረሰበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል የተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ስርዓት እንዲኖር ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመው፤ ይህን ተሳቢ ያደረገ የሎጂስቲክስ ስርዓት የመፍጠር ጉዳይ አጽንኦት እንደተሰጠው ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የሎጀስቲክስ ዘርፉን የሚያቀላጥፉ በርካታ ዘመናዊ ሲስተሞች እየለሙ መሆኑንም ጨምረው ጠቁመዋል።
በሎጂስቲክስ ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ ስራዎች በዘርፉ ያሉ አለም አቀፍ እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ስምምነቶችን የሚደግፉ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሎጂስቲክስ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አለም አቀፍ ደረጃዋን ለማሻሻል እንደሚያስችላትም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የተናገሩት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025