የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነች ነው - ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር)

Apr 15, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ በመስራት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ሶስተኛው የአፍሪካ ዌልዲንግ ፌዴሬሽን ጉባኤ በአዲስ አበባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው ላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት መሰረት በመሆኑ ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች፡፡


የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ እውቀት ወሳኝ በመሆኑ መንግስት የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማትን በማጠናከር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ለቴክኒክና ሞያ በተሰጠው ትኩረት በዘርፉ የሰለጠኑ በርካታ ሞያተኞች በኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራትም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸውን የሰው ሀይል፣ እውቀት እና ልምድ በመለዋወጥና በጋራ በመስራት እርስ በእርስ መማማር እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ በአፍሪካ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ ከሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡


የአፍሪካ ዌልዲንግ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሐመድ አብደል-አሊም በበኩላቸው የአፍሪካ ዌልዲንግ ፌዴሬሽን በስድስት ዓመታት ውስጥ ከ13 በላይ አባል ሀገራትን ለማፍራት በቅቷል ብለዋል።

የዌልዲንግ ዘርፍን በቀጣይ ለማሳደግ በሀገራት የኢንዱስትሪ ስትራቴጂዎችና በሙያ ትምህርት ስርዓቶች ውስጥ ማካተት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በሰው ሀይል ላይ ኢንቨስት ማድረግና የስልጠና መሰረተ ልማቶችን ማሻሻል ወሳኝ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል።


የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በበኩላቸው የዌልዲንግ ቴክኖሎጂ የዘመናዊ ኢንዱስትሪ መሰረት በመሆኑ ኢትዮጵያ በዘርፉ የልህቀት ማዕከል አቋቁማ በርካታ ተግባራት እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።

ዌልዲንግ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር በኩል ትልቅ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

የዌልዲንግ ሙያ የበለጠ ተፈላጊና ተወዳዳሪ እንዲሆን በኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።


ሶስተኛው የአፍሪካ ዌልዲንግ ፌዴሬሽን ጉባኤና አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ያላትን ተሞክሮ እንድታካፍል እና ልምድ ልውውጥ እንድታደርግ የሚያግዝ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) ናቸው ፡፡

16 የአፍሪካ ሀገራት እየተሳተፉበት የሚገኘው ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ እስከ ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ድረስ እንደሚቆይም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026