የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ከ260 በላይ የውጭ ባለሀብቶች በተፈቀዱ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተዋል- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

Apr 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ሚያዝያ 9/2017 (ኢዜአ)፡-የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ከ260 በላይ የውጭ ባለሀብቶች በተፈቀዱ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።


የኮሚሽኑ ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግመዋል።


በዘጠኝ ወራቱ የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ከማሻሻል ፣አዳዲስ ኢንቨስተሮችን ከመሳብና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር አመርቂ ውጤቶችን መመዝገባቸው ተገልጿል።


የማይክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ለውጭ ባለሀብቶች በተፈቀዱ የወጪ፣ ገቢ፣ ጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ሥራዎች ከ260 በላይ ባለሃብቶች በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳሳዩ ሪፖርቱ አመላክቷል።


ፍላጎት ካሳዩት መካከል የ78ቱ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 40 የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል።


በሌላ በኩል የውጭ ኢንቨስትመንትን ከመሳብ አንጻርም ስኬታማ ስራ መከናወኑም ነው የተገለጸው።


የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም ብልጫ ያለው ቢሆንም የተሻለ ስራ ማከናወን እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።


ከባለድርሻ አካላት ጋርም በተቀናጀ መልኩ ስራን በማከናወን እንዲሁም ለባለሀብቶች ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ረገድ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025