ሀዋሳ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፡-የተረጋጋ የበዓል ገበያ እንዲኖር የፍጆታ ምርቶች በማህበራት በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸውን የሲዳማ ክልል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ቦልካ ለኢዜአ እንደገለጹት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለማስቀረት አስቀድሞ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ለዚህም በማህበራት፣ በዩኒየኖችና በአርሶ አደሮች አማካይነት ለበዓል የሚሆኑ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ የተለያዩ እህሎች እንዲሁም ገብስ፣ ቀይና ነጭ ሽንኩርት፣ ቅቤ፣ አይብ፣ እንቁላል፣ ስኳር፣ ዘይትና ሌሎች ምርቶች ለገበያ መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡
እነዚህ የግብርና ምርቶች በክልሉ በተለዩ 35 የገበያ መዳረሻዎች መቅረባቸውን ጠቅሰው፣ በአጠቃላይ በማህበራቱ አማካይነት ለበዓል ገበያ 128 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እንቅስቃሴ ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ወጣት ምህረት ሲሳይ እና ወይዘሮ ባንችአማረ ለማ በበኩላቸው ከዚህ በፊት በከተማዋ በተዘጋጁ የመንገድ ዳር ገበያዎች ለበዓል የሚሆኑ የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመታቸውን ተናግረዋል።
በገበያው ለበዓሉ የተለየ የዋጋ ጭማሪ እንደሌለ ገልጸው ቀደም ሲል በነበረው ዋጋ ምርቶችን እየሸመቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአትክልት ምርቶችን ከማሳቸው አንስተው በሀዋሳ ከተማ በተዘጋጀ የገበያ ሥፍራ እያቀረቡ መሆኑን የገለጹት አርሶ አደር ሀያት ኑርሁሴንም፣ በገበያው ሁሉንም የአትክልት ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡
መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የዋጋ ጭማሪ እንደሌለ ገልጸው ቀይ ሽንኩርት፣ ቲማቲምና ድንች በኪሎ40 ብር እንዲሁም ነጭ ሽንኩርት በ320 ብር እየተሸጠ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ከመደበኛ ገበያ በተወሰነ መጠን ቅናሽ እንዳለው ነው ያመለከቱት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025