ሰቆጣ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር መጪው የመኸር ወቅት የሰብል ልማት ከተረጂነት ለመላቀቅ በሚያስችል መንገድ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
በብሔረሰብ አስተዳደሩ የ2017/2018 የምርት ዘመን በሚከናወነው የመኽር እርሻ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመንገድ መምሪያ ሃላፊ አቶ ፀጋው እሸቴ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በመጨው መኸር ወቅት አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ በትኩረት ይሰራል።
ለዚህም አርሶ አደሩን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማሸጋገር የሚያስችሉ ስራዎች በቅድመ ዝግጅት ወቅት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ለማሳካትም የማዳበሪያ አቅርቦት፣ በመስመርና በኩታ ገጠም መዝራትን ጨምሮ ሌሎችም የምርት ማሳደጊያ ግብአቶች እንደሚተገበሩ ጠቁመው፤ አርሶ አደሩና ባለሙያው በጊዜ የለኝም መንፈስ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በበኩላቸው፤ ከተረጂነት ለመላቀቅ የተሻሻለ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማስፋት ስራ ላይ በማተኮር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመጪው መኽር 120ሺህ 638 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በመተግበርም እስካሁን በሄክታር ሰባት ኩንታል ምርት የሚገኘውን ወደ 13 ኩንታል ከፍ ለማድረግ ግብ መያዙን ገልጸዋል።
ለዚህምለመጪው መኽር ከሚያስፈልገው 50ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 32ሺህ ኩንታል በማቅረብለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የብሔረሰብ አስተዳደሩ አመራር አባላትና የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025