ጋምቤላ፤ሚያዝያ 10/2017(ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል በትንሳዔ በዓል ሰሞን የኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በአገልግሎቱ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኔትወርክ መሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጥጋቡ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከበዓሉ ጋር ተያይዞ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።
በበዓሉ ወቅት የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር እንዳይከሰት ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር የሚነካኩ የዛፍ ቅርንጫፎችን የማስተካከል፣ የአገልግሎቱ ሰራተኞችን ግንዛቤ ማሳደግና የመስመሮችን ደህንነት የማየት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
መስሪያ ቤቱ በበዓሉ ወቅት በድንገት ለሚያጋጥም የኃይል መቋረጥ ችግርም ፈጣን ምላሽና የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ኮማንድ ፖስት ማቋቋሙንም ገልጸዋል።
የኤሌክትሪክ መቋረጥ ሲያጋጥም ደንበኞች ችግሩን በፍጥነት ማሳወቅ እንዲችሉም ተጨማሪ የስልክ መስመር መዘርጋቱን ተናግረዋል።
አቶ ደጀኔ አክለውም፥ ህብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲጠቀም ኃይልን በሚቆጥብና የአጠቃቀም መደራረብ ችግር በማይፈጥር መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025