ደብረ ማርቆስ፤ ሚያዚያ 13/2017(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል የወተትና የሥጋ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ እንስሳትና አሳ ሃብት ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ቡድን መሪ አቶ ጤናው ወንድም አማሽ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ አርሶ አደሩን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በእንስሳት ሃብት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ።
በበጀት ዓመቱ የግብርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከ54ሺህ በሚበልጡ ላሞች ላይ የዝርያ ማሻሻል ሥራ ለመስራት ታቅዶ በ9ኝ ወሩ ከ19ሺህ በላይ ላሞች ላይየማዳቀል ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል።
በኮርማ በማስጠቃትና በዘመናዊ የማዳቀያ መንገዶች ከተዳቀሉ ላሞችም ዝርያቸው የተሻሻሉ ከ9ሺህ 400 በላይ ጥጆች መወለዳቸውን አብራርተዋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።
ዝርያቸው የተሻሻሉ ለሞችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ የሌማት መርሀ ግብርን እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆን ያስታወቁት ቡድን መሪው፣ የዝርያ ማሻሻል ሥራው የአካባቢው ላሞች በቀን ይሰጡት የነበረን ከሁለት ሊትር በታች የወተት ምርት በቀን ከ10 ሊትር በላይ ወተት ለማምረት ማስቻሉን ገልጸዋል።
በሥጋ ምርትም ዝርያቸው ከተሻሻሉ ከብቶች በአማካይ እስከ 30 ኪሎ ግራም ጭማሬ እንዳለው ጠቁመው፣ ይህም የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድገው አስገንዝበዋል።
በአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ ነዋሪ አቶ ሙሉሰው ማስረሻ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ከዚህ በፊት ከተዳቀሉ ሁለት ላሞች በቀን እስከ 18 ሊትር የወተት ምርት በማግኘት ከሽያጩ ገቢያቸውን እያሳደገ መምጣታቸውንተናግረዋል።
ከወተት ልማት ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማሳደግም ሁለት ላሞቻቸውን በተሻሻሉ ኮርማዎች ማዳቀላቸውን ጠቁመዋል።
በእዚሁ ወረዳ የጉዳለማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ደርብ ካሳ በበኩላቸው ዝርያቸው የተሻሻሉ ላሞችን በማርባት ከወተት ሽያጭ በተጨማሪ ጥጆችን በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከዞኑ እንስሳትና አሣ ሃብት ተጠሪ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳያው በዞኑ ቁጥራቸው እስከ 200 ሺህ የሚደርሱ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው እንስሳት ይገኛሉ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025