
ጊምቢ፤ሚያዝያ፤15/2017(ኢዜአ)፦በምእራብ ወለጋ ዞን የተፈጠረው አስተማማኝ ሰላም ለምርት ዘመኑ የግብርና ልማት ስኬት መልካም እድል የፈጠረ መሆኑን የአካባቢው አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በዞኑ ለ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እየተሟላና ከወዲሁ እየደረሳቸው መሆኑንም አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል።
የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤትም ለአርሶ አደሮች ማዳበሪያ በወቅቱ ተደራሽ የማድረግ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
በምእራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች በዞኑ የተፈጠረው አስተማማኝ ሰላም ለምርት ዘመኑ የግብርና ልማት ስኬት መልካም እድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
በአካባቢው የተጠናከረና አስተማማኝ ሰላም በመፈጠሩ የግብርና ልማት ስራዎችን በወቅቱ ለማከናወን ያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።
በዞኑ የላሎ አሳቢ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አስቴር ተርፋሳ፤ ለምርት ዘመኑ የግብርና ስራ የአፈር ማዳበሪያ ከወዲሁ እየቀረበ በመሆኑ ለምርታማነት የሚያበቃ መሆኑን ገልጸዋል።
የማዳበሪያ የክፍያ ስርዓትም በዲጂታል የታገዘ በመሆኑ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽ የሆነ አሰራር የፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።
በሖማ ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር ላሜሳ ሀብቴ፤ ለመኸሩ የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ ለምርታማነታችን ጥሩ እድል ይሆናል ብለዋል።
በዞኑ አሁን ላይ ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩም አርሶ አደሩ ትኩረቱን ሙሉ ለሙሉ ወደ ግብርና ስራ ማድረጉን ተናግረዋል።
ለመኸር እርሻ የሚያስፈልጋቸውን የአፈር ማዳበሪያ መግዛታቸውን የተናገሩት ደግሞ የላሎ አሳቢ ወረዳ ኢናንጎ ካሊ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ገመቹ ፍቅሩ ናቸዉ፡፡
በአካባቢው ያለው የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ የግብርና ልማትን በወቅቱ ተንቀሳቅሶ መስራት የሚያስችልና ለምርታማነት ጥሩ መሰረት መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህም ባለፈ ለማዳበሪያ ክፍያ የተዘረጋው የዲጂታል ክፍያ ስርዓት በርካታ ችግሮችን የፈታና ቀልጣፋ አሰራርን የዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን የምርጥ ዘርና የአፈር መዳበሪያ ፍላጎት ሰብሳቢ ባለሙያ ወይዛሮ በአምላክ አንዷለም ለመኸሩ ከ340 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማደባሪያ ለአርሶ አደሮች በመዳረስ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ለመኸር ወቅቱ ከታቀደው ከ95 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በየወረዳዎቹ ማከፋፈያ ጣቢያዎች መድረሱን ጠቁመው፥ከዚህም እስከሁን ከ47 ሺህ 749 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ደርሷል ብለዋል።
በዞኑ በተያዘው 2017/18 ምርት ዘመን መኸር ወቅት ከ416 ሺህ 965 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች በመሸፈን ከ13 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026