ደሴ፤ ሚያዚያ 15/2017(ኢዜአ)፦ ግብር በወቅቱ በመክፈል የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ በደሴ ከተማ የሚገኙ ግብር ከፋዮች ገለጹ።
ከለውጡ ወዲህ በከፈልነው ግብር በከተማችን ተጨባጭ ልማት ተመልክተናል፤ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ሲሉም ግብር ከፋዮቹ ተናግረዋል።
"ግብር ለሀገር ክብር" በሚል መሪ ሃሳብ የደሴ ከተማ የግብር ንቅናቄ እና ዕውቅና መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።
ከመድረኩ ተሳታፊ ግብር ከፋዮች መካከል ወይዘሮ አዋጋሽ የሻው በሰጡት አስተያየት፤ ግብርን በታማኝነት በመክፈል ሀገራዊ ግዴታን በመወጣት ልማት እንዲፋጠን ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በተሰማሩበት የስራ መስክ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግብር መክፈላቸውን ጠቁመው፤ የከፈሉት ግብር ከሌሎች ጋር ተዳምሮ በከተማችን የተለያዩ ልማቶች እየተከናወኑ እንደሆነ ማረጋገጥ ችያለሁ ብለዋል።
ቀጣይም ተገቢውን ግብር በመክፈል የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
ሌላዋ ግብር ከፋይ ወይዘሮ ሶፊያ አሊ፤ በተሰማሩበት የሸቀጣሸቀጥ ንግድ የተጣለባቸውን ከ12ሺህ ብር በላይ ግብር በወቅቱ መክፈላቸውን ተናግረዋል።
ግብር በወቅቱ መክፈላችን ደግሞ በከተማው የተለያዩ ልማቶች በወቅቱ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ተደስተናል፣ የግብር ጠቀሜታን በውል እንድንረዳ አድርጎናል ነው ያሉት፡፡
ቀደም ሲል የምንከፍለው ግብር የት እንደደረሰ እንኳ ማወቅ አንችልም ነበር ያሉት ወይዘሮ ሶፊያ፤ ከለውጡ ወዲህ በከፈልነው ግብር ተጨባጭ ልማት ተመልክተናል ብለዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ሚካኤል በበኩላቸው፤ በከተማው የተሻለ ገቢ በመሰብሰብ የከተማውን ልማት ማፋጠን እንደተቻለ ገልጸዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአንድ ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቁመው፤ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡
ሆኖም ከተማው ከሚመነጨው ኢኮኖሚ እና ከህብረተሰቡ የልማት ፍላጎት አኳያ ከዚህ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚገባ አንስተው፤ ለዚህም በንቅናቄ ግብር የመሰብሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችና ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ በቅንጅት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ናቸው፡፡
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ገቢ የመሰብሰብ አቅም እየጨመረ በመምጣቱ በከተማው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰፋፊ የልማት ስራዎችን በማከናወን ለአገልግሎት ማብቃት ተችሏል ብለዋል፡፡
በመድረኩ የክልል፣ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራር አባላት፣ ግብር ከፋዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፤ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025