የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮ ቴሌኮም እና ቪዛ ኢንክ ኩባንያ በዲጂታል ፋይናንስ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

Apr 27, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 16/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮ ቴሌኮም እና የአሜሪካው የክፍያ ካርድ አገልግሎት ኩባንያ ቪዛ ኢንክ በዲጂታል ፋይናንስ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከአሜሪካው ቪዛ ኢንክ ኩባንያ የደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንትና ኃላፊ ሚካኤል በርነር ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።


ውይይቱ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ላይ አዳዲስ የትብብር ዕድሎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ ላይ ተቋማቱ ነሐሴ 2016 ዓ.ም በጋራ ይፋ ያደረጉት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዋሌት ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ እና በቪዛ ዳይሬክት እንዲሁም በቴሌብር ረሚት በኩል የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ሐዋላ አገልግሎቶች የሚገኙበት የአፈጻጸም ደረጃ ቀርቧል።

በሐዋላ አገልግሎቶቹ የተመዘገበው አበረታች አፈጻጸም እና በተለይም ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የገበያ እድል ማደጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በዓለም አቀፍ ሐዋላ አገልግሎቶች ላይ ቀጣይነት ያለው ማሻሻያ እየተከናወነ መሆኑም ተነስቷል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ቴሌብር ለአካታች እና ተደራሽ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ ነው ብለዋል።

ቴሌብር ከቪዛ ዓለም አቀፍ ኔትወርክ ጋር በመጣመር አዳዲስ ፈጠራ የታከለባቸው የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብ የሚቻልባቸው ዕድሎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የቪዛ ኢንክ የልዑካን ቡድን በጋራ ተግባራዊ የተደረጉት ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ስኬት በማድነቅ የገበያውን ከፍተኛ አቅም መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

ተጨማሪ የትብብር ዕድሎችን በመፈተሽ የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያሰፋና በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ባህል ግንባታ ትብብር ላይ የሚሰራ የጋራ ቡድን ለማቋቋም መስማማታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ተቋማት ራሳቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...

Feb 28, 2025

<p>በክልሉ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው</p>

ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...

Feb 28, 2025

<p>ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...

Feb 28, 2025

<p>በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቅ እየተሰራ ነው</p>

ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...

Feb 24, 2025