
ደብረብርሃን፤ሚያዚያ 18/2017(ኢዜአ)፦በደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪዎች የሚለለቁትን ፍሳሽ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማከሞ ለመስኖ ልማት ለማዋል የተጀመረው ተግባር መጠናከር እንዳለበት የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት አሳሰቡ።
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ዘመናዊ የማጣሪያ ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ አክሞ በሚለቀው ውኃ በ119 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ዛሬ በከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በጉብኝት ላይ እንደገለጹት፥ በከተማ አስተዳደሩ በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።
ከነዚህ ኢንዱስትሪዎች የሚወጣውን ፍሳሽ በአግባቡ በማከም ለመስኖ ልማት በማዋል የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የሚለቀውን ፍሳሽ በቴክኖሎጂ በማከም ለመስኖ ልማት በማዋል ለሌሎች ፋብሪካዎች ተሞክሮ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል።
የዛሬው ጉብኝት ዋና አላማም የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለአካባቢ ጥበቃና ልማት ያበረከተውን አስተዋጽኦ ለአርሶ አደሩ ለማሳወቅና ሌሎች ፋብሪካዎችም ተግባሩን እንዲከተሉ ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ መርሻ አይሳነው በበኩላቸው፥ በያዝነው በጋ ወራት 4 ሺህ 527 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ 2 ሺህ 413 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ እየለማ ይገኛል።
ከለማው ሰብልም ከ144 ሺህ 900 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የታቀደውን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ፍሳሹን በማጣራት ለመስኖ ልማቱ እንዲውል ያበረከተው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በዳሽን ቢራ ፋብሪካ የማህበረስብ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታነህ ዝቄ እንዳሉት ፋብሪካው በሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ብለዋል።
ፋብሪካው በትምህርት፣በጤና፣በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በመስኖ ልማት ላይ በማተኮር ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አሁን ላይም ከፋብሪካው የሚወጣው ፍሳሽ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በማጣራት አካባቢውን ከብክለት ነጻ የማድረግና ተጣርቶ በሚለቀቀው ውሃ አርሶ አደሮች በመስኖ እንዲጠቀሙ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አርሶ አደር አሸናፊ በላይነህ እንደገለጹት፥ የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከፋብሪካው የሚለቀውን ፍሳሽ በማከም ንጹህ ውሃ በመልቀቁ ታርሶ የማያውቅ መሬታቸውን በበጋ ስንዴ ማልማት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
በአንድ ሄክታር መሬታቸው ላይ በመስኖ ያለሙት የበጋ ስንዴ ሰብል የፍሬ አያያዙ ጥሩ በመሆኑ ከ45 ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚያገኙ ጠቁመዋል።
በጉብኝቱ ላይም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የአካባቢው አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል።
እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...
Jul 27, 2026
ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...
Jul 21, 2026
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...
Jun 27, 2026
ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...
Jun 26, 2026