አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከብሪታንያ የዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ባሮንስ ቻፕማን ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች የተወያዩት በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው እኤአ የ2025 የዓለም ገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ የጸደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።
ውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
በቀጣይም ሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ሊሰሩባቸው የሚችሉባቸውን ዕድሎች ማስፋት ላይም ውይይት አድርገዋል።
አቶ አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለውን የኢኮኖሚ ሪፎርምና ያስገኘውን ውጤት፣ እየገጠሙ ያሉ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች፣ የኢትዮጵያ አዎንታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ሪፎርሙን የበለጠ ውጤታማ የሚያደርጉ እንዲሁም በሁለትዮሽ ትብብር ቀጣይነት ባለው መልኩ መደረግ ስለሚገባቸው ድጋፎች ለሚኒስትሩ ገለጻ ማድረጋቸውም ተመላክቷል።
የብሪታንያ የዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ባሮንስ ቻፕማን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ መሆኑን አድንቀዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የምታደርገውን ጥረትም እንዲሁ።
ኢትዮጵያ የጀመረችው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ሀገራቸው በዓለም አቀፍ የልማት ትብብር በኩል ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል።
የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር በማስፋት ከልማት ትብብር ባለፈ በኢንቨስትመንት በንግድና በፋይናንስ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውም ተመላክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ተቋማቸውን ለተገልጋዮች ምቹ ሊያደርጉ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድ...
Feb 28, 2025
ወልቂጤ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሬት ምልከታ እና በኮሙኒኬሽን ሳ...
Feb 28, 2025
ጋምቤላ ፤የካቲት 17/2017 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ነባር ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ እርም...
Feb 24, 2025